የህግ እና ፍትህ ሰራዎችን በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ ሰራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቆመ

የህግ እና ፍትህ ሰራዎችን በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ ሰራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቆመ

ሀዋሳ፡ ጥር 28/2016 ዓ.2016 (ደሬቴድ) የህግ እና ፍትህ ሰራዎችን በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ ሰራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቅሟል።

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህግ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 የ6ወራት አበይት ተግባራት አፈፃፀም ዙርያ ምክክር አካሄደ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህግ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዱንጋ ናቁዋ  የህግ እና ፍትህ ሰራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ ሰራዎችን ማጠናከር  እንደሚገባ ገልፀዋል።

በ6ወራት ውስጥ 11ሺህ 76 መዝገቦች ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑን ገልፀው በ1 ሺህ 996 ቱ ላይ ከባድ 315 መካከለኛ እና 5929 በቀላል ወንጀል ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አቤነዘር ተረፈ በግማሽ ዓመቱ በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ ክርክር ከሩብ አመቱ የዞረእና አዲስ የቀረበ 8 ሺህ 992 በአጠቃላይ  10,648 መዝገቦች 7658መዝገቦች ውሳኔ ያገኙ፣ 1ሺህ309 መዝገቦች በፍርድ ቤት በእርቅ  እንዳለቁ ጠቁመዋል።

5ሺህ 5መቶ 60 መዝገቦች የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው፤ 296 መዝገቦች በነፃ ስንብት እንዲሁም 493 መዝገቦች ከሳሽ እና ምስክር ባለመቅረቡ መዘጋቱን አመላክተዋል።

የይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ 769 መዝገቦች ለችሎት ክርክር ቀርበው 315 ቱ ይግባኝ ጠይቀው 232 ውሳኔ ያገኙ ሲሆን 454 መዝገቦች በተከሳሾች ቀርበው109 ውሳኔ ማግኘቱንም አቶ አቤነዘር ተናግረዋል።

አክለውም የ50 ሰዓት ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ከመስጠት አኮያ የቅም ውስንነት ማስረጃ ላቀረቡ138 የህብረተሰብ ክፍሎች የጥብቅና አገልግሎት መስጠት መቻሉን ተናግረዋል።

የሙስና ጉዳዮችን አስመልክቶ በ12ቱ ዞኖች የተለያዩ አገልግሎት ፈላጊ የህብረተሰብ ክፍሎች በቃል እና በጽሁፍ የቀረቡ 800 አቤቱታዎች በመመሪያው መሰረት ምላሽ መሰጠቱን ኃላፊው ገልፀዋል።

የተመዘበረ ና የተመለሰ የመንግስት ሀብትን በተመለከተ በግማሽ ዓመቱ 9 ሚሊዮን 744ሺህ 817 የተመዘበረ ሲሆን 5 ሚሊዮን 396ሺህ 432ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን እና 4ሚሊዮን 348ሺህ 385 በፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ እንዳለ አመላክተዋል።

የቋሚ ኮሚቴ አባላትም ክልሉ በአዲስ መልክ እንደመደራጀቱ የነበሩ ክፍተቶችን ተቋቁሞ  በዚህ መልኩ ለተግባራዊነቱ መትጋቱ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በቀጣይም ዐቃቤ ህግ እጅ ላይ የሚቆዩ መዝገቦች፣ ይቅርታ የሚሰጣቸው ታራሚዎችን ከማረም እና ከማነፅ አኳያ፣ እና የማረሚያ ቤት አያያዝ ጉዳይ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

ዘጋቢ፡ ሰለሞን አላሶ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን