የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ለስራ ጉዳይ ወደ ውብቷ ወላይታ ሶዶ ገብተዋል።
ሚኒስትሯ ወደ ውቢቷ ወላይታ ሶዶ ሲገቡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በወላይታ ሶዶ የሚካሄደው 9ኛው ኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን እየጎበኙ ናቸው ሲል የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል፡፡
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች