ጠንካራ ባህላዊ መዋቅር በመኖሩና ህዝቡም ተግባራዊ በማድረጉ ሥርዓቱ እንደ ችግር መፍቻነት እያገለገለ እንደሚገኝ የጌዴኦ የባህል አባት አባገዳ ቢፎሚ ዋቆ ገለጹ
የአካባቢው ማህበረሰብም ከአባገዳው የሚተላለፉ ባህላዊ መመሪያዎችን ተቀብለን በመተግበራችን ተጠቃሚ ሆነናል ሲሉም ተናግረዋል።
ብሔሩ በሚተዳደርበት ባህላዊ በ”ባሌ” ስርዓት መሠረት ከየአካባቢው የተውጣጡ የህዝብ እንደራሴዎች ስለ ህዝቡ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊውም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች በመመካከር በአባገዳው አማካይነት አዋጅ እንዲተላለፍ የሚደረግ ጠንካራ ባህላዊ መዋቅር ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ አባገዳው ገልጸዋል።
የሚተላለፉ አዋጆች ወይም መመሪያዎች የህዝብን የዕለት ተዕለት እንቅሰቃሴን መሠረት ያደረጉ በመሆናቸው ለተግባሮቻቸው አጋዥ እንደሚሆኑም አስረድተዋል።
ከጥንት ጀምሮ እሰከዛሬ ጠብቀው በመምጣታቸው በአካባቢው ሠላምን፣ ልምላሜን፣ አንድነትንና ሌሎች ትሩፋቶችን ለመጎናጸፍ መቻላቸውን የተናገሩት አባገዳው ስርዓቱ ዛሬም እነዚህን ፋይዳዎች ለማስቀጠል የጎላ ሚና አንዳለውም አስገንዝበዋል።
የዞኑ ነዋሪዎችም ከአባገዳው የሚተላለፉ መመሪያዎችን ተቀብለን በመተግበራችን ተጠቃሚ ሆነናል ሲሉም ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/