በ2016 በተደረገዉ ንቅናቄ በክልል ደረጃ 75 በመቶ የጤና መድን አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የጤና መድህን ያለበትን ደረጃ የገመገመ ሲሆን እስከአሁን በአባልነት የተመዘገቡት ቁጥራቸዉ ወደ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን በመሆኑን በክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ ታመነ ገልጸዋል።
በዚህም መክፈል የሚችሉ ራሳቸዉ እንደሚከፍሉና መክፈል የማይችሉት ተለይተዉ በወረዳ፣ በዞንና በክልሉ መንግስት የሚሽፈን መሆኑንም ተናግረዋል።
ከነባር አባላት እድሳት አኳያ እስከአሁን ባለው ሂደት በዞኖች ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡት ኮንታ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ መሆናቸው ተመላክቷል።
በተካሄደዉ ግምገማ መሻሻሎች መታየታቸዉን የገለፁት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በአንድ ሳምንት ውስጥ በተካሄደዉ ንቅናቄ የጤና መድህን አባልነት ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ አባይነሽ ወራቦ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የዘርፉን ተግባራት በተገቢው ለማሳካት ከምንጊዜውም በተሻለ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ