የግብርና ሚኒስቴር የግማሽ አመት አፈጻጸሙን በአርባምንጭ ከተማ በዛሬው እለት ይገመግማል

ሀዋሳ፡ ጥር 25/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የግብርና ሚኒስቴር፣ የተጠሪ ተቋማትና የክልሎች የ2016 በጀት የግማሽ አመት አፈጻጸሙን የሚገመግም መድረክ በአርባ ምንጭ ያካሂዳል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) አርባምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በጋሞ አባቶች ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይለማርያም ተስፋዬና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ለቀጣይ ቀናት በሚደረገው በዚሁ የግምገማ መድረክ የሁሉም ክልሎች የግማሽ አመት አፈፃፀምን ጨምሮ ቀጣይ የዘርፉ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ: ወንድወሰን ሽመልስ