አለም ባንክ ማህበራዊ ጥበቃ ላይ ለሚከናወኑ ተግባራት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠ
ሀዋሳ፡ ጥር 24/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) አለም ባንክ ማህበራዊ ጥበቃ ላይ ለሚከናወኑ ተግባራት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡
በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ሁርያ አሊ እንደገለጹት መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በተለይም ደሃና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሁሪያ አክለውም በተለይም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ውሎና አዳራቸው ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎች ቁጥር እና ተያያዥ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ማህበራዊ ትስስርንና የቤተሰብ ሚና ማሳደግ፣ ማህበራዊ ጥበቃን በዘላቂነት ፋይናንስ ማድረግ፣ ውጤታማ የማህበራዊ ዋስትና ሽፋንን ማስፋፋት ዜጎች ክብራቸው ተጠባቆ የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ መፍጠር የሚኒስቴር መስሪ ቤቱ አላማና ራዕይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ደሃና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እንደ አለም ባንክ ካሉ ድርጀቶች ጋር ዘላቂ የሆነ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን ለመገንባት እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ውጤታማነት የሚረዱ ተጨማሪ ድጋፎችን እንደሚያስፈልጉም አስታውቋል።
በአለም ባንክ የአፍሪካ አካባቢ የማህበራዊ ጥበቃና ስራ አተገባበር ስራ አስኪያጅ (practice manager) ሮበርት ቼዝ እንደገለጹት አለም ባንክ ህዝብን ያማከለ አካሄድ በመከተል በመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት፣ የምግብ ዋስትና እና የተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍል ችግሮችን በመፍታት ላይ ያተኮረና የረጅም ጊዜ የልማት እቅድን ይዞ መቅረቡንም ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የአለም ባንክ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎች የሚሰጠውን የማህበራዊ አገልገሎት በዲጂታል መልክ ለማድረግ እንዲሁም አሰራሩን ዘመናዊ ለማድረግ የሚሄድበትን መንገድ እንደሚደግፉ አስታውቋል፡፡
ምንጭ ፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ