የሕዝቦችን መሠረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት የሚያስችል የፖለቲካና  አደረጃጀት ሥራዎች መሠራቱን የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሕዝቦችን መሠረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት የሚያስችል የፖለቲካና አደረጃጀት ሥራዎች መሠራታቸውን የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በጠበላ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት እንደ ዞን ላለፉት ስድስት ወራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ የፖለቲካና አደረጃጀት ሥራዎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ ገለጹ።

የተመዘገበው ስኬት በፓርቲው በሳል አመራር፣ በመላው አመራር፣ አባላትና ደጋፊዎቹ ጥንካሬና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በጤናው፣ በግብርናው እንዲሁም በትምህርት፣ በስራ ዕድል ፈጠራና ኑሮ ውድነትን ለማቃለል የተከናወኑ ተግባራት ጉድለት ቢኖርም ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑንም አንስተዋል።

በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች አመራሩ ወቅታዊና መደበኛ ተግባራትን በንቅናቄ በመምራት ያስመዘገበው ስኬት በጥንካሬ መገምገሙንም አቶ አሳምነው ጠቅሰዋል።

አመራሩ የህዝቡን አዳጊና መሠረታዊ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

በየደረጃው የሚገኘው አመራርና አባል “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ሀሳብ የተሰጠው ስልጠና ተጨባጭ ውጤት እየተገኘ ይገኛል ያሉት አቶ አሳምነው በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን መለየት ሀብት በመፍጠር ብልፅግናን ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

መድረኩ ጥንካሬን ለማጎልበት፣ ጉድለቶችን ለማረምና ለቀጣይ ተልዕኮ አመራሩ ዝግጁ እንዲሆን የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የሚወጣበት መድረክ ነው ብለዋል።

ባለፉት በስድስት ወራት የነበሩ ጥንካሬዎችን በማጽናትና በማስፋት እንዲሁም ጉድለቶችን በመለየት ቀጣይ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የወላይታ ዞን የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን አለማየሁ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ደገፉ፣ የፓርቲ ስራ አመራር እና የወረዳና ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ዘርፉ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  ዘጋቢ፡ በቀሌች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን