በቤንች ሸኮ ዞን የተጀመረው የዘንድሮ የተቀናጀ የተፋሰሰ ልማት ሥራ ፕሮግራም ላይ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ደግፌ ኩድን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዞኑ በጊዲ ቤንች ወረዳ በዲዙ በቀበሌ ዲክ ንዕስ ተፋሰሰ ላይ በይፋ የተጀመረውን ዘንድሮ የተቀናጀ የተፋሰሰ ልማት ሥራን ያስጀመሩት የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን እንደገለፁት ከ2003 ዓመተ ምህረት የተጀመረው በአሁን ሰዓት የህብረተሰቡ አመለካከት እየተቀየረ በመምጣቱ ለውጥ መታየት መጀመሩን ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ቅድመ አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩት የተፈጥሮ ደን መመናመንና ለም መሬት እየተሸረሸረ መምጣቱ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን እንድንሰራ ያደረገ በመሆኑ በቀጣይም በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አክሊሉ ተገኝ በበኩላቸው በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ የታየው አብሮነት እያንዳንዱ አርሶ አደር በየጓሮው በመተግበር የልማቱ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።
የዞኑ ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ በበኩላቸው የተለያዩ ዘርፈ ብዙና የኢኮኖሚ ጠቃሚነት ያላቸው ከ1 ሚሊየን በላይ ችግኞች እንደሚሳኩና በሚኖረው ተከታታይ 30 ቀናት ሁሉም ሚናቸውን እንዲወጡም አስገንዘበዋል።
ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በቤንች ሸኮ ዞን ጊዲ ቤንች ወረዳ በተጀመረበት ወቅት የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ሀብታሙ ካፒተን የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ደግፌ ኩድንና የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ፀጋዬ ታደሰን ጨምሮ የክልል፣ የዞን እንዲሁም የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የሀይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ