ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በወንዶ ገነት ከተማ እየተሰሩ የሚገኙትን መሰረተ ልማቶች ተዘዋውረው ተመለከቱ
ሀዋሳ፡ ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የተመራ ልዑክ በወንዶ ገነት ከተማ እየተሰሩ የሚገኙትን መሰረተ ልማቶች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማው የተሰራውን የመሰረተ ልማት ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት እንደገለፁት የህዝባችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ከመፍታት ባሻገር የብልፅግና ጉዞን ለማሳለጥ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራችንን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
በጉብኝቱ መርሃ ግብር የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን፣ የክልልና የዞን የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ምንጭ ፡ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ