አንትሮሽት” ወይም የእናቶች የምስጋና አመታዊ ክብረ በዓል የማጠቃለያ መርሃግብር በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ በድምቀት እየተከበረ ነው
ሀዋሳ፡ ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) አንትሮሽት” ወይም የእናቶች የምስጋና አመታዊ ክብረ በዓል የማጠቃለያ መርሃግብር በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
“አንትሮሽት” ቃሉ ጉራጊኛ ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ የእናቶች የምስጋና ቀን ማለት ነው።
“አንትሮሽት” በዞኑ አለም ‘የሴቶች ቀን’ እየተባለ ማክበር ከመጀመሩ አስቀድሞ በባህላዊ መልኩ ይከበር እንደነበር በስነሥርዓቱ ላይ ተወስቷል።
መድረኩ ይህንን እንቁ ባህላዊ እሴት ለማሳደግና ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ እና ወጥ በሆነ መልኩ ለማክበር አላማ ያደረገ ነውም ተብሏል።
ከዚህ በዓል ጎን ለጎንም በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የልጃገረዶች ቀን ወይም ነቐ በዓል በድምቀት መከበሩን የተጠቀሰ ሲሆን ይህም የጉራጌ ማህበረሰብ ለሴት ልጅና ለእናት ያለው ክብር ልዩና ከፍተኛ መሆኑን እንደሚያሳይ ነው የተገለፀው፡፡
የአንትሮሽት” ወይም የእናቶች አመታዊ ክብረ በዓል በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሰሞኑን ሲከበር አንደነበረ የተገለፀ ሲሆን በዓሉ በዛሬው ዕለት እየተከበረ የሚገኘው ደግሞ በዞን አቀፍ ደረጃ እንደሆነ ተመላክቷል።
በበዓሉ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ መሃመድን ጨምሮ ከክልል፣ ከጉራጌ ዞንና ምስራቅ ጉራጌ ዞን፣ ከወልቁጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ መሀመድ ሽሁር – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ