የእርሻ ስራችን ከጉልበትና ከጊዜ ብክነት የወጣ ባለመሆኑ የሥራ ባህላችንን መቀየር አለብን ተባለ
በኮሬ ዞን “የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በማዘመን በግብርና ሥራችን ምርታማነትን እናሳድጋለን” በሚል መርህ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ፣ የበልግ እና የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የኮሬ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ የግብርና መምሪያ ኃላፊ እና የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አስታረቀኝ አንደባ ለተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ባሉበት ወቅት እንደገለጹት፣ ዞኑ በተፈጥሮ ጸጋ የታደለ፣ በሰንሰለታማ ተራሮች የተከበበና የበርካታ መስህቦች ባለቤት ነው።
ግብርና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ አስታረቀኝ፣ ሁሉንም በአግባቡ መመለስ የሚቻለው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ሲቻል ነው ብለዋል።
ባለፈው የምርት ወቅት ላይ በተገኘው የግብርና ምርት የዋጋ መረጋጋት እንደታየ የገለጹት ሀላፊው፣ የተፋሰስ ልማትን መሥራት የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የሚረዳ በመሆኑ በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የቡና ምርታማነትንም ለማሳደግ የጉንደላ ስራ፣ የችግኝ ና ጉድጓድ ዝግጅትና ሌሎች ተግባራትን በመፈጸም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ በአግባቡ ለማግኘት መሥራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
የእርሻ ስራችን ከጉልበትና ከጊዜ ብክነት የወጣ ባለመሆኑ የሥራ ባህላችንን መቀየር አለብን ሲሉ ገልጸዋል።
ቴክኖሎጂን በአግባቡ ያለመጠበቃችን ምርታማነታችንን ጎድቷል ያሉት አቶ አስታረቀኝ 50 በመቶ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፍ ለገበያ ማቅረቡም በትኩረት ሊወሰድ ይገባል ብለዋል።
የሥርዓተ ምግብን ማሻሻል ጤናችንን መጠበቅ በመሆኑ ማረጋገጥ አለብን ብለው አመራርን ጨምሮ ሁሉም ቁርጠኛ እንዲሆን አሳስበዋል።
በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ፣ ከዝናብ እጥረት በመላቀቅ በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የተመሠረተ የመኖ ልማት ማስፈፋት፣ የአፈር ለምነትና እርጥበትን ማሻሻል፣ ምርታማነትን ማሳደግና የእንስሳተት ሀብት ልማትን ውጤታማ ማድረግ እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አካባቢና ኢኮኖሚን ለመገንባት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል።
የተፈጥሮ ሀብታችንን ማልማት ሀገራዊ እድገትን በዘላቂነት ለማስጠል ያለውን ፋይዳ በመረዳት
ከ2003 ዓም ጀምሮ በተሰሩ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ታይተዋል ብለዋል።
በ2016 ለሚሠራው የተፋሰስ ልማት የሰው ሀይል ፣ የእርሻ መሳሪያ ፣ የንዑስ ተፋሰስ ልየታና ዲዛይን የተደረገ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
ዘጋቢ : እስራኤል ቅጣው – ከይ/ጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ