የሴቶች የንቅናቄ መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳን አስረክባለሁ” በሚል መሪ ቃል የሴቶች የንቅናቄ መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የክልሉና የዞን አመራር አካላት እንዲሁም በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሴቶችና በዞኑ የሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሴቶች ሊግ አካላት ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ቆይታ የሀገርን ሰላምና ልማት በማረጋገጥ ረገድ ሴቶች መወጣት በሚገባቸው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል።
ዘጋቢ: ሳሙኤል መንታሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ