ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገቡ
ሀዋሳ: ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የዘንድሮውን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በይፋ ለማስጀመር ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ገብተዋል::
በመርሀግብሩ ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማ ሱሩርና ሌሎችም የክልል እና የልዩ ወረዳ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ