ሀዋሳ፡ ጥር 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ፋቱ ሀይድራናን የዩኒዶ ኢትዮጵያ(UNIDO,Ethiopia) የስራ ኃላፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ስለ ድርጅቱ ድጋፍ ስኬቶችና በስራ ሂደት ስላጋጠሙ ችግሮች ኢንዲሁም ቀጣይ ስለሚደረጉ የትብብር ማዕቀፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
ሚኒስትሩ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የአምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ዘርፉ በተሻለ ሁኔታ የሚጠበቅበትን ሀገራዊና አለማቀፋዊ እድገት ያሳካ ዘንድ ድጋፉ በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ የስራ ሪፖርት በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ እና ቀጠናዊ ዳይሬክተር ኦሬሊያ ፓትሪዢያ ካላብሮ ቀርቦ ውይይት መደረጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
More Stories
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ምረቃ
በኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ደረጄ ዱጉማ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የሥራ ጉብኝት አደረጉ
በህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየው አንድነት እና ትብብር በልማቱ እና በሰላሙ ላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ