ከ800 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የቡና ኮንፍረንስና ኤግዚቪሽን እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።
የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ከ800 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የመጀመሪያው “የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ” እና 20ኛው የአፍሪካ ኮፊ አሶሴሽን ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ከጥር 28 እስከ የካቲት 2/2016 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን የ25 ቡና ላኪ አፍሪካ ሀገራትና የቡና ገዢ ሀገራት የግብርና ሚኒስትሮች ተጋብዘዋል።
በኮንፍረንስና ኤግዚብሽኑ ድርጅቶች ምርታቸውን እንደሚያስተዋውቁ፤ ዝርዝር ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው እና በጅማና ሃዋሳ የጉብኝት መርሃግብር እንደሚኖር ተገልጿል።(ኢፕድ)

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ