ሀዋሳ፡ ጥር 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ለወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ500 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ የማይክሮስኮፕ እና 25 አይነት መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁስ ያካተተ ነው።
የተደረገው ድጋፍ በሆስፒታሉ የሚሰጠውን የሴቶችና ህጻናት የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ግልጋሎት ለማጠናከር የሚውልነው ተብሏል፡፡
የፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኃላፊና የፍትሐ ብሄርና ወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ገብሬ አስፋው የአንድ ማዕከል አገልግሎት (One Stop Center) አላማ ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በአንድ ጣሪያ ስር የተቀናጀ የጤና፣ የፍትህ፣ የሰነልቦናና ማህበራዊ አገልግሎት መስጠት እና በቀጣይ የሚያሰፈልጋቸውን አገልግሎቶች በቅብብሎሽ ስርዓት እንዲያገኙ ማድረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢክማ ሁሴን ከቢሮው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ