ሀዋሳ፡ ጥር 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) አራት ፌስታል አደንዛዥ እፅ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያዘዋውሩ የተገኙ አምስት ግለሰቦች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ለቡ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-26732 አ.አ በሆነ ተሽከርካሪ በአራት ትልልቅ ፌስታል ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ እፅ ጭነው ሲያዘዋውሩ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተሽከርካሪውን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎችን ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ለወንጀል መንስኤ በሆኑና አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ጫት መቃሚያ ቤቶች እንዲሁም ቁማር ቤቶች ላይ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ተከታታይነት ያለው እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።
በተለይም ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የመከላከሉ ስራ የሚፈለገውን ውጤት ማስገኘት እንዲችል የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ