ሀዋሳ፡ ጥር 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በቡርጂ ዞን የሶያማ ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተደራሽነትን ለማፋት እየሠራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡
በቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ አስተዳደር በማህበራዊ ክላስተር የጤና ዩኒት አስተባባሪ አቶ ኮሹ ሁቃ በከተማ አስተዳደር ስር ባሉ 6 ቀበሌያት የሚኖሩ የማህበረሰብ አካላትን ያካተተ 1ሺህ 7 መቶ 43 በራሳቸው ከፍለው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
መንግስት ወጪ የሚሸፍንላቸው 3 መቶ 32 ነዋሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ 2 ሺህ 74 ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል፡፡
ዩኒቱ መታወቂያ ያገኙ ቤተሰቦች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሶያማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ጋር ውል መግባቱን ኃላፊው ተናግረዋል።
የተቀሩት የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በከተማው ጤና ኤክስተንሽን ሙያተኛ ሲስተር ስመኙሽ አለማየሁ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ከአጠቃቀም አንፃር የግንዛቤ ችግር እንዳለባቸው በማንሳት በተለይም ውል ከተገባበት ጤና ተቋም ውጪ አገልግሎት የመጠየቅ ሁኔታዎች መኖራቸውን አንስተዋል።
ወ/ሮ ስሌ አያና እና ቦጋለች ጫንያለው በጋራ በሰጡን አስተያየት የማህበረሰብ ጤና መድን አገልግሎት በርካታ ጥሩ ነገሮች ያሉት መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ : አብዶ አያላ- ከይ/ጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በበጀት አመቱ ከማህበረሰቡ በመቀናጀት የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስከበር ከፍተኛ ስራ መስራቱን ገለጸ
ጽዱ ከተማ ለመፍጠር የህብረተሰብ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
ፖሊስ ከመደበኛ ስራዉ ጎን ለጎን ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ የሚያካሂደዉን የልማት ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ