በደቡብ ኦሞ ዞን ሣላማጎ ወረዳ የ2016 ዓ.ም የተፋሰስ ልማትና የበልግ ሥራዎች ንቅናቄ በሃና ከተማ ተካሄዷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካድሱ ካሻሌ እንደገለፁት፤ የተፋሰስ ልማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፤ ብዝሃ ሀብቶችን ለማስጠበቅ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እንደሚረዳ ገልፀው በእስከዛሬው ሂደትም የአርሶ አርብቶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ለወጥ ያመጣ እንደሆነ አመላክተዋል።
አክለውም የሥነ-አካላዊ እና ሥነ-ህይወታዊ ሥራዎችን በማጠናከር በተያያዘም የበልግን ሥራ በውጤታማነት ለመፈፀም ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡም አሳስበዋል።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት የተፋሰስ ልማት ጥናትና ዲዛይን ባለሙያ አቶ ያንተአለ ላቀው በዘንድሮ 2016 ዓ.ም የተፋሰስ ልማት ሥራ አጠቃላይ 32ሺህ አባወራ፣ እማወራ እና ወጣቶችን በማሳተፍ 24ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል።
በመድረኩም መነሻ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሄዶበታል።
ከተሣታፊዎች መካከል አቶ ሉች ናበጋስ ፤ ጌታሁን ማሞ እና ሌሎችም በሰጡት አሰተያየት ከዚህም ቀደም በነበሩ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ምርታማነታቸው እንደጨመረ ገልፀው በዘንድሮውም በተሻለ መንገድ ለመስራት በንቅናቄ ተሳትፈው እንደሚያሳትፉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ደፋሩ ስፍታዬ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
በጎፋ ዞን ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ክልላዊ የ6ኛ ክፍል ፈተና እየተሰጠ ነው
የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በመመለስ በኩል ከመንግስት ጥረት ባለፈ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና የጎላ መሆኑን የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ተናገሩ
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን አስጀመሩ