የዳራሮን በዓል ለማክበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን በጌዴኦ ዞን የወናጎ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ገለጸ

የዳራሮን በዓል ለማክበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን በጌዴኦ ዞን የወናጎ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥር 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በወረዳው ለሚከበረው የብሔሩ የአዲስ ዓመት መቀበያ ዳራሮን በዓልን ለማክበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን በጌዴኦ ዞን የወናጎ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ።

ዘንድሮ ላይ የጌዴኦ ብሔር መልከዓ ምድር አያያዝ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ በተሻለ መልኩ ለማክበር እንዳነሳሳቸው የተናገሩት የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ሽፈራው ናቸው።

በዓሉ የራሱን ይዘት እና እሴት ጠብቆ እንዲከበርና የዘመኑ ትውልድም ግንዛቤ ሊጨብጥ በሚያስችል መልኩ ዝግጅት መደረጉን ነው ኃላፊው የገለጹት።

ይህም ስኬታማ እንዲሆን አብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው ተግባሩን ሲመሩ ቆይተዋል ያሉት አቶ ወንድማገኝ አሁን ላይ ዝግጅቶቹ በስኬት ተጠናቋል ብለዋል፡፡

በዓሉ በነገው ዕለት “ኡዴሳ ሶንጎ” በተባለው ባህላዊ ስፍራ አባገዳው፣ የባህል ሽማግሌዎች፣ የመንግስት አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የዞኑ ህዝብ በተገኙበት በድምቀት እንደሚከበር ገልጸዋል።

ዘገቢ:- አማኑኤል ትዕግስቱ- ከይርጋ ጨፌ ጣቢያችን