የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት 13ኛ ዓመት 1ኛ ዙር መደበኛ ጉባኤው ማካሔድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ ጥር 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ግድባችን፤ የእድገትና ብልጽግና ጉዞአችን ጮራ!” በሚል መሪ ሃሳብ የተጀመረው ጉባኤ፥ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ም/ቤት ያለፉ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ላይ እየመከረ ነው።
ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ፍቃዱ ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ሀገር የህዳሴ ግድብ ግንባታውን በ2017 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ባለበት ማግስት የሚካሄድ ጉባኤ በመሆኑ ልዩ መነቃቃት የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ አሼቦ በበኩላቸው፥ ከነባሩ ክልል እስከ አዲሱ ክልል ድረስ የተከናወኑ የእቅድ አፈጻጸም አቅርበው ዝርዝር ውይይት እየተካሔደ ነው።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
በክረምቱ ወቅት የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ጊዜያቸውን በአግባቡ ለመጠቀም ከማስቻሉም በላይ ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ዝግጅት ከፍተኛ እገዛ እያደረገላቸው መሆኑን በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች ገለፁ
ብሔራዊ የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ መያዝ የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚጠቅም ተገለጸ
በክልሉ በ2018 በጀት አመት ከ336 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መቻሉ ተገለጸ