በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ የሚሰጡ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን ለመምረጥ የሚያስችል የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው
በመድረኩ ላይ ወጣቶች፣ መምህራን፣ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ከልዩ ወረዳው የተወጣጡ 100 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው በውይይቱ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ከእያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል አጀንዳ የሚሰጡ ሁለት ሁለት ተወካዮች ከአንዳንድ ተጠባባቂ ጋር ይመርጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ አጎን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ