የጋርዱላ ዞን ህዝቦች የፊላና ባህል ፌስቲቫል እንዲሁም የዘመን መለወጫ “ሀይሶት ህርባ” በዓል በዞኑ ማዕከል ጊዶሌ ከተማ በነገዉ ዕለት በደማቅ ስነ-ስርዓት ይከበራል
ሀዋሳ፡ ጥር 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጋርዱላ ዞን ህዝቦች የፊላና ባህል ፌስቲቫል እንዲሁም የዘመን መለወጫ “ሀይሶት ህርባ” በዓል በዞኑ ማዕከል ጊዶሌ ከተማ በነገዉ ዕለት በደማቅ ስነ-ስርዓት ይከበራል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታን ተከትሎ ወደ ዞን መዋቅር የተሸጋገረዉ የጋርዱላ ዞን ይፋዊ ምስረታም ይካሄዳል።
በዛሬው ዕለት በዓሉን ምክንያት በማድረግ “የምሁራን አንድነትና ህብረት ለጋርዱላ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የሰላምና ልማት ሲምፖዚየም መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የአከባቢዉ ተወላጅ ምሁራን፣ የሐይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በጋርዱላ ዞን የዲራሼ፣ ኩሱሜ፣ ማሾሌና ሞስዬ አራት ብሔረሰቦችን ጨምሮ መላዉ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ይኖራል።
ዘጋቢ፡ ድልነሳዉ ታደሰ

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ