እንደ ምክር ቤቱ የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዱንጋ ናኩዋ ገለፃ በዞኑ በፍትህ ስርአቱ የሚከናወኑ የቅንጅት ስራዎች በጠንካራ ጎናቸው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
በሳውላ ማረሚያ ተቋም አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አፈፃፀማቸው መልካም ቢሆንም ሊስተካከሉ የሚገባቸው ስራዎች በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አስታውቋል።
በዞኑ በወንጀል አስከፊነት እንዲሁም መረጃን ወቅታዊ ከማድረግ አኳያ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ያለው ቋሚ ኮሚቴው በተለይ ለፀጥታ ችግር ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ ሁነቶች ላይ ዞኑ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
እንደ ጎፍ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ፍንታዬ በቋሚ ኮሚቴው የተደረጉ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች ቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት አጋዥ መሆናቸውን ገልፀው ሊስተካከሉ ይገባል የተባሉ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ቅንጅታዊ ስራ ሊጠናከር ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህንም ለማገዝ የዞኑ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ቃለአብ ፀጋዬ
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ