ሁሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ ውጤታማ ለመሆን በመትጋት ለጋራ ለውጥ ሊረባረብ እንደሚገባ የጌዴኦ አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ ገለፁ
ሀዋሳ፡ ጥር 14/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ)ሁሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ ውጤታማ ለመሆን በመትጋት ለጋራ ለውጥ ሊረባረብ እንደሚገባ የጌዴኦ አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ ገለፁ፡፡
ይህም የተባለው የብሔሩ ዘመን መለወጫና የምስጋና ዳራሮ በዓል በጌዴኦ ዞን ጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር በተከበረበት ነው፡፡
የጌዴኦ ብሔር አባገዳ ቢፎሚ ዋቆ ዳራሮ የአንድነት የወንድማማችነትና የምስጋና በዓል መሆኑን ጠቁመው ትውልዱ በየተሰማራበት የሙያና የሥራ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን መትጋት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
አከባቢው ያለው መሬት ጠባብ በመሆኑ ትውልዱ በትምህርት ላይ እንዲያተኩርና የሥራ ባህሉን እንዲያጎለብት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት አባገዳ ቢፎሚ ፈጣሪ የአከባቢው ሠላም ጠብቆ እንዲያቆይ ምርታማነት እንዲጨምር ፈጣሪ የተሻለ ዝናብ ለአከባቢው እንዲሰጥ ፈጣሪን ተማፅኗል፡፡
በዞኑ የጨጨለቅቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተስፋዬ ፈይሳ ለብሔሩ ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ለሆነው ዳራሮ በዓል በዞኑ ለሚገኙና አጎራባች አከባቢዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፏል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ አሁን ያለውን የዞኑን ሰላም በዘላቂነት በመጠበቅ መንግስት የያዛቸውን ዕቅዶች ከዳር ለማድረስና የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ሁሉም በጋራ እንዲረባረብ አሳስቧል፡፡
ዘጋቢ፡ ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ