የደቡብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደሮች ቀን በዓል በዲመካ ከተማ እየተከበረ ነው

ሀዋሳ፡ ጥር 12/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኦሞ ዞን 10ኛው አርብቶ አደሮች ቀን በዓል “አርብቶ አደርነት የምስራቅ አፍርካ ህብረ ቀለም” በሚል መሪ ቃል በዲመካ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ ወላይቴ ቢቶ፣ የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ ዳርጌ ዳሼን፣ የአካባቢው የህዝቦች ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች፣ የበዓሉ ባለቤት የሆኑ አርብቶ አደሮች፣ ከአጎራባች ኬንያ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

በመድረኩ በቀጣይ በአርብቶ አደሮች አካባቢ ሰፋፊ ልማቶችን ይበልጥ ለማረጋገጥ ልዩ ውሳኔ እንደሚተላለፍና በዘርፉ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና እንደሚሰጣቸውም ከወጣው መርሐ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን