የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተቸገሩ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ ጥር 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከፍተኛ ፈተና እንደሆነባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የባህር በር የሌላት ኢትዮጵያም ችግሩን ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ መሰረት ጥረት እያደረገች እንደሆነ ማስረዳታቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑካን ቡድናቸው በዑጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።
More Stories
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ተናገሩ
በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ ያለውን የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራ በታቀደው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ