የከተሞች ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የነዋሪዎች ሚና ላቅ ያለ ነው – በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክሊሉ አዳይ
ሀዋሳ፡ ጥር 09/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የከተሞች ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የነዋሪዎች ሚና ላቅ ያለ ነው ሲሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክሊሉ አዳይ አስታወቁ።
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ሁለንተናዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በ32 ከተሞች ላይ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያና በሚገጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
ከእነዚህ ከተሞች መካከልም የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ውይይትም ተጠቃሽ ነው።
የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ስጦታን ብቻ ይዞ መቀጠል ህዝቡን ተጠቃሚ እንደማያደርግ ገልፀው ያሉ የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት ጥረት ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
ለዚህም የከተማዋን ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገጥ የገቢ አሰባሰብ ሂደትን ማዘመን ይጠበቃልም ብለዋል።
ከከተማዋ በሚመነጭ ገቢ ብቻ የምትተዳደረውን የአርባምንጭ ከተማን ከሌሎች አቻ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ ትሆን ዘንድ የነዋሪው ተሳትፎ ወሳኝ ነውም ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም ከ 2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ የታቀደ መሆኑን ያስታወሱት ከንቲባው ለዚህም የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን ታማኝነት እንዲያረጋግጥም ጠይቀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የውሃና ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክሊሉ አዳይ በበኩላቸው መንግስት በይበልጥ ከአጭር ጊዜ ወዲህ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ ለማድረግ ባደረገው ርብርብ ለውጦች መምጣታቸውን ያስታወሱት ኢንጅነር አኪሊሉ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ያለውን የህዝብ ቁጥር ዕድገትን የሚመጥን ሥራም ይጠበቃልም ብለዋል።
በዚህም በአርባምንጭ ከተማም የሚሰተዋለው የመልማት ፍላጎት የሚመጥን ተግባር መሠራት አለበትም ብለዋል።
ከተሞች ላይ የሚፈለገውን የልማት ተግባራት ለመከወን የህዝቦች ድጋፍ ያስፈልጋል ያሉት የቢሮው ኃላፊው በገቢ አሰባሰብ ረገድ ያሉ ሂደቶች ከተማዋን የሚመጥ አይደለምም ብለዋል።
በየተቋማት የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ጉድለትን ማዘመን ላይ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራም ይገኛልም ያሉት ኢንጅነር አክሊሉ የአከባቢውን የሠላም ሁኔታን ለመልካም አጋጣሚ መጠቀም ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር ነውም ብለዋል።
በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ተግባራት ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ሲታከልበት ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ከተማዋን ለማልማት ቁርጠኛ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ: በኃይሉ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ