አመራሩና የግብርና ከአርሶ አደሩ ጋር በቅንጅት ከሰሩ እንደ ሀገር የተያዘው የብልፅግና ጉዞ ከተያዘለት ወቅት አስቀድሞ ይሳካል – አቶ ጥላሁን ከበደ
አመራሩና የግብርና ከአርሶ አደሩ ጋር በቅንጅት ከሰሩ እንደ ሀገር የተያዘው የብልፅግና ጉዞ ከተያዘለት ወቅት አስቀድሞ ይሳካል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ተናገሩ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት እና የበልግ አዝመራ ስራ በይፋ ተጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለፁት በግብርናው ዘርፍ አመራሩና የግብር ባለሙያው ከአርሶ አደሩ ጋር በቅንጅት ከሰሩ የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ከተያዘለት ወቅት አስቀድሞ ይሳካል ብለዋል።
ነገር ግን ይሄን ለማሳካት መልፋትንና መትጋትን ይጠይቃል።
ግብርናን ጨምሮ ቱሪዝም፣ የማምረቻው ዘርፍ ፣ማዕድን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መሠረት መሆናቸው ጠቅሰው በሁሉም ዘርፎች ለተሻለ ውጤት በጋራ መስራት ይገባል በማለት አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መልካም በአየር ፀባይ ያለው ሰፊ የእርሻ መሬቶቸና በቂ የውሃ ሀብት ያለው በመሆኑ ይሄን የተፈጥሮ ፀጋ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ልማድ 21% ብቻ ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ይሄም ምርትና ምርታማነትን በእጅጉ እየጎዳው በመሆኑ እርምት ይወሰዳል ብለዋል።
በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተያዘው አመት ወደ 50 በመቶ ለማድረስ ይሰራል ብለዋል።
አመራሩ በትንንሽ ውጤቶች ከመርካትና ከመዘናጋት በመውጣት ለተሻለ ውጤት እንዲዘጋጁም ጥሪ አቅርበዋል።
ለወጣቶች የግብርናው ዘርፍ የስራ ዕድል መፍጠር እንዳለበት ያነሱት አቶ ጥላሁን ሰፋፊ ማሳ ወስደው በስራ ላይ ያሉ በለሀብቶች በተቀመጠው ስታንዳርድ በመሠረት እራሳቸውንም ሆነ ሀገራቸው መርዳት አለባቸው ነው ያሉት።
ከደረጃ በታች እየሰሩ ባሉ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
በተፋሰስ ልማት ዘርፍ የተያዙ ዕቅዶችም በተያዘላቸው መስፈርት መሠረት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደ መሬት ለማውረድ ይሰራል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ወደብ ለማልማት ስምምነት ላይ መድረሷ ለግብርናው ዘርፍ መልካም ዕድል ይዞ ይመጣል በማለት ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ጀማል የሱፍ
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ