በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችን ማልማትና መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የአሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለፀ

በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችን ማልማትና መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የአሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለፀ

ሀዋሳ፡ ጥር 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችን ማልማትና መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የአሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል፡፡

መምሪያው የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ እና ቀጣይ የቀሪ ስድስት ወር ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር የባለድርሻ አካላት እና የህዝብ ክንፍ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የአሪ ዞን ምክትል አስተዳደርና ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ እንደገለፁት፤ በየአካባቢው በርካታ የተፈጥሮ የቱሪስት መስህቦች በመኖራቸው ይህንን ማልማትና መጠበቅ ከሁሉም ይጠበቃል።

መመሪያው በዞኑ ስር ያሉ እምቅ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማስተዋወቅ እየሠራ ስለመሆኑ የገለፁት የአሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ ኤልያስ ቃሾ ናቸው።

መድረኩ በመምሪያ በኩል የተከናወኑ ተግባራትን እያደመጠ የሚገኝ ሲሆን ሰፊ ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን