የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል አርባምንጭ ከተማ ገቡ
ሀዋሳ፤ ጥር 2/2016 ዓ.ም. (ደሬቴድ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ለመንግስታዊ ስራ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ወደ አርባምጭ ከተማ ሲገቡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለሚኒስትሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ሚኒስትሩ በአርባምንጭ ቆይታቸው በኢትዮጵያ ታምርት መርሃ ግብር የኢንዱስትሪ ፖሊሲና ተኪ ምርት ስትራቴጂ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ይሳተፋሉ።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ
More Stories
ተቋማት በተደራጀ እቅድ እንዲመሩ ጥሪ ቀረበ
”ሠላምን ማፅናት ለክልሉ ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ መካሔድ ጀመረ
በሀዲያ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ