“በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል” – አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈፃፀም ላይ የተደረገ የመስክ ምልከታ ሪፖርት በዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቧል።
ሪፖርቱ አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰን ጨምሮ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚዲያ ተቋማት መሪዎች እና የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በተገኙበት ቀርቧል።
በዚሁ ጊዜ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ- ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ እንዳሉት በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ነው ያሉት።
ቋሚ ኮሚቴው በሲዳማ፣ በሀረሪ ፣ በቤንሻጉል ክልሎች እንዲሁም በኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት በመገኘት የምክክር ኮሚሽኑ ተግባር እና ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ምልከታ ማድረጋቸውን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።
በቀረበው ሪፖርት መነሻነትም ውይይት እየተደረገበት ነው።
ምንጭ ፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/