በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ የሚገኘው የጋልማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ተመረቀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ኮሌጁን በይፋ መርቀው ሲከፍቱ እንዳሉት ኮሌጁ በብርቱ ክትትል በ8 ወር ውስጥ ተጠናቋል ብለዋል::
ኮሌጁ አምራች ዜጎችን እንዲፈጥር በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የመንግስት እጅን የማይጠብቁ ለሌሎችም የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ወጣቶች መፍጠር ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ህንፃው ፍሬያማ የሚሆነዉ ተማሪዎች በፍላጎታቸው ተመዝግበው እንዲማሩ በማድረግ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስትም ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ