ከ500 ኪሎ ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ ጭኖ ከሻሸመኔ ወደ ኬንያ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጸ
መነሻውን ሻሸመኔ ያደረገው ኮድ 3 ሰሌዳ ቁጥር 22382 ኦሮ FSR የጭነት መኪና 525 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እፅ ጭኖ ወደ ኬንያ ሲጓዝ በደረሰ ጥቆማ ታህሳስ 14 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 6 ሰአት ገደማ በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ኤልጎ ቀበሌ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ኦንቶ አስረድተዋል።
ብሔራዊ መረጃና ደህንነት እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የገለጹት አዛዡ የቅንጅት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው ህብረተሰቡም ለሚሰጠዉ ጥቆማ አመስግነዋል።
አክለውም ወንጀለኞች የወንጀል ድርጊታቸውን በየጊዜው እያዘመኑና ውስብስብ እያደረጉ በመሆኑ ፖሊስም የፍተሻና የምርመራ ሂደቱ ዘመናዊና ጠንካራ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
በኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ግንባታ እና ተያያዥ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የጠቅላላ ተቋራጮች እና የአገልግሎት ተቋማት ትጋትና ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማህበራዊ ጫናዎችን ለመከላከል የኢኮኖሚ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላላት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለፀ
ትምህርት ቤቶች የዉስጥ ገቢያቸዉን በማሳደግ የግብዓት ችግሮችን በመቅረፍ ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢን መፍጠር እንዳለባቸዉ ተገለፀ