የአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ለፍራፍሬ ምርት እና ሌሎች ዓይነተኛ የዘርፉ ምርቶችን የሚያካትተውን የሆርቲካልቸር ልማት ሥራን ለማስፋፋት ያለመ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ለፍራፍሬ ምርት እና ሌሎች ዓይነተኛ የዘርፉ ምርቶችን የሚያካትተውን የሆርቲካልቸር ልማት ሥራን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ፡፡
በመስኖ የተደገፈ እና ምርቱ የላቀ የሆርቲካልቸር ሥራ ለማከናወን የተደረገው ጥረት አስደናቂ ውጤቶችን በማሳየት ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡
የዚህ ውጤት ዋና ማሳያ በፓፓያ ምርት ላይ የታየው ምርታማነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
More Stories
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበች ላለችው የዕድገት ጉዞ ቀጣይነት የትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ሲል የጋሞ ዞን አስተዳደር አሳሰበ
በትምህርት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጽንቶ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገለፁ
በኮንታ ዞን ጳጉሜን 1 – የጽናት ቀን በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል