በከተማ ግብርና የነዋሪዎች ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ታሕሳስ፡ 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በከተማ ግብርና በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል ሲል የከሌ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዕርባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የከተማ ነዋሪዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተክትሎ መንግስት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲመግብና የቤት ወጪውን እንዲሸፍን ለማስቻል በከተማ ግብርና ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ተመልክቷል።
በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ 02 ቀበሌ የእርባታ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ከበቡሽ ደኖ በከተማ ግብርና በሬ በማድለብ፣ ፍየል በማሞከት፣ ንብ በማንባት፣ በዶሮ ሀብት ልማትና የውጭ ዝርያ በማሻሻል ላይ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰማርተው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ገበያን ከማረጋጋት አንጻር የከተማ ግብርና ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ያነሱት ባለሙያዋ፥ ሁሉም ህብረተሰብ በእርባታ ሆነ በሌሎች ዘርፎች ላይ በመሳተፍ በመኖሪያው፣ በጓሮ እና በማሳው አምርቶ በመጠቀም የራሱን ኢኮኖሚ በማሻሻል ኑሮውን መደጎም አለበት ብለዋል።
በተሰማሩበት ሁሉ ውጤታማ እንዲሆኑ ተከታትለን በማስተማር፣ በመምከርና እንዴት መሥራት እንዳለባቸው በማሳየት ውጤታማ እንዲሆኑ በማገዝ ላይ መሆናቸውን ወ/ሮ ከበቡሽ ጠቁመዋል።
አቶ በቀለ ባጋጆ እና ጥላሁን ሳጅን በከተማ ግብርና ንብ በማነብና ከብት በማደለብ ሥራ ላይ ከተሰማሩት መካከል ሲሆኑ፥ ሥራውን ከጀመሩ ወዲህ ኑሯቸውን ተረጋግተው መምራት እንደቻሉ ጠቁመው፥ የባለሙያ ክትትልና ድጋፍ እንዳልተለያቸውም ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ለምለም ኦርሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበች ላለችው የዕድገት ጉዞ ቀጣይነት የትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ሲል የጋሞ ዞን አስተዳደር አሳሰበ
በትምህርት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጽንቶ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገለፁ
በኮንታ ዞን ጳጉሜን 1 – የጽናት ቀን በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል