የዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያ በኢሠራ ወረዳ ከሁለት መቶ በላይ ላሞችን ዝሪያ የማሻሻል ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ ገለጸ
አርሶ አደር በቀለ ባዶሬ፣ አርሶ አደር ሹራቤ አበራ፣ አርሶ አደር አበራ አገሬ፣ እና ሌሎችም አርሶ አደሮች ከባለሙያዎች ባገኙት ግንዛቤ መሠረት ላሞቻቸውን እያዳቀሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
በወረዳው የእንስሳት ሀኪም እና አዳቃይ ባለሙያ አቶ እንድሪያስ ደርጫ በበኩሉ አርሶ አደሮቹ እንዲህ ተረባርበው እንስሳቶቻቸውን ለማዳቀል መፈለጋቸው ያለሰለሰ የግንዛቤ ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
በወረዳው የአዳቃይ ሙያተኛ እጥረት መኖሩን የገለፀው ሙያተኛ ይህንን ተገንዝበው ከዞኑ በተውጣጡት ሙያተኞች መታገዙ በርካታ ላሞችን ለማዳቀል መቻሉንም አክሏል ።
የኢሠራ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት የእንስሳት ዝሪያ የሥራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ አስራት ዶሻ በበኩላቸው ይህ ተግባር ከሌማት ትሩፋት አንዱ መሆኑን ተናግረው የወተተ መንደር በተለዩ 36 መንደሮች ውስጥ የሚገኙ 280 ላሞች እንዲዳቀሉ ማድረጋቸውን ገልጸዋል ።
ለወተት ምርት ምቹ የሆኑ አከባቢያዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ሲሉ የገለፁት ደግሞ የዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻያ ባለሙያ እና የዘመቻው አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደነቀ ደስታ ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡ አሸናፊ ግዛው – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ