ሀገሪቱን አሁናዊ በሆኑ አለም አቀፍ ጉዳዮች ጋር ማስተሳሰር ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይጠበቃል – በአርባ ምንጭ የስልጠና ማዕከል የሚገኙ ሠልጣኞች

ሀገሪቱን አሁናዊ በሆኑ አለም አቀፍ ጉዳዮች ጋር ማስተሳሰር ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይጠበቃል – በአርባ ምንጭ የስልጠና ማዕከል የሚገኙ ሠልጣኞች

ሀዋሳ፡ ሕዳር 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሀገሪቱን አሁናዊ በሆኑ አለም አቀፍ ጉዳዮች ጋር ማስተሳሰር ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ይጠበቃል ሲሉ በአርባ ምንጭ የስልጠና ማዕከል የሚገኙ ሠልጣኞች ተናገሩ

ወቅቱን በመዋጀት የአከባቢን እምቅ ሀብት ወደ ምንዳ መቀየርም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ስለመሆኑም ሠልጣኞቹ ተናግረዋል።

“ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ በሀገሪቱ 17 ማዕከላት ከ21 ሺህ 800 በላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች 3ኛውን ዙር ሥልጠና እየተከታተሉ ይገኛል፡፡

በአርባ ምንጭ የስልጠና ማዕከል ተገኝተው ስልጠናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የአፋር፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያና የሀረሪ ክልል የስራ ኃላፊዎች እንደተናገሩት ራሳቸውን ከወቅቱ ዓለም ዓቀፍ ሁኔታ ጋር በመዋጀት ሀገሪቱ ያላትን እምቅ ሀብት አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ከጊዜ አጠቃቀም ጀምሮ የሰው፣ የውሃ፣ የማዕድንና የመሬት ሀብቶችን በአግባቡ መጠቀም ለነገ የሚያድር የቤት ሥራ አይደለም የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በዚህ ረገድ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው የሚሳተፉ አመራሮች የአከባቢያቸውን ተሞክሮ ለሌሎች በማጋራትና ከሌሎች በመጋራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባቸዋልም ብለዋል፡፡

ከስልጠናው በዘለለ ህዝቡ ከመሪው ጋር በመቀናጀት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማሳካት የወቅቱ ሥራ ነው ያሉት ሠልጣኞቹ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የኤክስፖርት ምርቶችን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በሀገሪቱ ለ3ኛ ዙር የሚሰጠው የመንግስት አመራሮች ሥልጠና እስከ ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚዘልቅ ታውቋል፡፡

ዘጋቢ፡ በኃይሉ ሙሉጌታ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን