“ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የመንግስት አመራሮች ስልጠና በአርባምንጭ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል
የደቡብ ኢትዮጵያዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደተናገሩት የሀገሪቱን ቀጣይ የብልፅግና ጉዞን ማሳካት የሚችሉ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ያስፈልጋሉ።
አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥትም የክልሉን ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ማመዛዘንና በፍጥነት ቀድሞ መገኘት የሚችል አመራር በሚሻበት ወቅት ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።
በአርባምንጭ ከተማ የሚሰጠውን የአመራሮች ስልጠና ለመውሰድ የመጡ አንግዶች በጋሞ አባቶች እና በህዝቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ዘጋቢ: በኃይሉ ሙሉጌታ- ከአርባምንጭ
More Stories
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ #ደሬቴድ፣ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም
የጤናው ዘርፍ አገልግሎት ለማጠናከር የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ