የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ ህደር 13 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ አስታወቁ
በዝግጅቱ ዙሪያ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የክልሉ ተወላጅ አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት እየተደረገ ነው።
በአዲስ አበባ እና በፌዴራል ተቋማት ለሚገኙ የክልሉ ተወላጅ አመራሮች የእስካሁኑን ቅድመ ዝግጅቶችና የይፋዊ ምስረታ ዓላማዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል።
በህዳር 13ቱ ይፋዊ ምስረታ ላይ ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ተሳትፎና ይሁንታ የሚያደርጉበት እንደሚሆን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ህደር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የክልሉ ይፋዊ ምስረታ የተለያዩ ክልሎችና ተቋማት ድጋፍና አጋርነት የሚገልጹበት እንደሚሆን አቶ ጥላሁን አስታውቀዋል።
የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹ በአብይና ንኡሳን ኮሚቴዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
ህደር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚካሄደው በዚሁ ይፋዊ ምስረታ የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ተቋማት አመራሮች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 12 ዞኖችን ይዞ የተዋቀረ እና በ6 ማዕላት የተደራጀ ክልል መሆኑ ይታወቃል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚባክነውን የህዝብና የመንግሥት ሀብት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
ቅንጅታዊ አሠራርን በማስፈን ጥምር ደን መጠበቅ፣ ማስፋትና መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ
የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በማዘመን የዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ