አዲስ የተደራጀዉ የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ሕብረተሰቡ በቅርበት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ለማሳካት በትጋት እንደሚሠራ አስታወቀ

አዲስ የተደራጀዉ የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ሕብረተሰቡ በቅርበት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ለማሳካት በትጋት እንደሚሠራ አስታወቀ

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሎስንዴ ሎኛስዋ እንደገለፁት አዲስ የተደራጀው የደቡብ ኦሞ ዞን ሕብረተሰቡ በቅርበት የልማት ትሩፋቶችን የሚያገኝበትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችንም ለማሳካት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አባልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ በበኩላቸው የሕዝቡን አብሮነት በማጠናከር፣ ሕብረተሰቡ የልማት ተጠቃሚ የሚሆንባቸውን ስልቶች በመቀየስ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማለኮ ያቀረቧቸዉ ዕጩ የደቡብ ኦሞ ዞን መምሪያ ኃላፊዎች ሹመት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በሐመር ወረዳ ከሚኖሩ ብሔረሰቦች መካከል የካራ ብሔረሰብ ባህላዊ አልባሳት በምክር ቤቱ ፀድቋል።

ባህላዊ አልባሱ የብሔረሰቡን ማንነት ገላጭ በሆነ አግባብ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።

ለ3 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ጉባኤ የአስተዳደር ምክር ቤት እና የዞኑ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድና ረቂቅ የበጀትና የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

በጉባኤዉ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወላይቴ ቢቶን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ፡ ዳኜ ጥላሁን – ከጂንካ ጣቢያችን