ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የትምህርት ቤት መሰረተ-ልማቶችን የማሻሻል መርሃ-ግብር ላይ በንቃት እየተሳተፉ መሆናቸውን የካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር የሚሆን ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል፡፡
ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ ያለመ ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ መሠረት በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ ገቢ የማሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በጊምቦ ወረዳ በየሞ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ደረጃ ለማሻሻል በንቃት እየተሳተፉ ከሚገኙት ነዋሪዎች መካከል አቶ ደሳለኝ ተሾመ እና አቶ እንግዳ ሀይሌ የሚገኙ ሲሆን፥ የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለማሻሻል ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ዮሃንስ ከበደ በበኩላቸው ለበየሞ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህብረተሰቡ ከ580 ሺህ ብር በላይ በማዋጣት ደረጃ የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን ገንብቶ ወደ ማጠናቀቅ መድረሱን አንስተዋል፡፡
የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ መለሰ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚሆን ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ጠቁመዋል፡፡
አሁንም ህብረተሰቡ በመረሃ-ግብሩ ላይ በንቃት በመሳተፍ የዜግነት ግዴታው እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ ጫካ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/