የደሬቴድ ዲጂታል ሚዲያ የጥቅምት 15/2016 ዓ.ም የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች፡-

የደሬቴድ ዲጂታል ሚዲያ የጥቅምት 15/2016 ዓ.ም የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች፡-

👉በውጊያ ከማሸነፍ የላቀው በሰላም ማሸነፍ በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ኃይል በሰላም፣ በድርድርና በውይይት ኢትዮጵያን በማፅናት ታላቅ ሀገር ለልጆቻችን ለማሸጋገር መትጋት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስገነዘቡ፡፡

👉116ኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ተከበረ፡፡

👉በተለያዩ ወቅቶች ሠላማችንን ለማደፍረስ እና ሀገር ለማፍረስ የተነሱ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን በመመከት ሀገርን ከትውልድ ወደ ትውልድ ያሸጋገሩ ጀግኖች ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡

👉የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ባወጣው መግለጫ “ለሀገራችን መክፈል ያለብንን ሁሉ ዋጋ በመክፈል የኢትዮጵያን ሠላም እና ዕድገት አፅንተን እናሥቀጥላለን” በማለት ገለጸ፡፡

👉በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራው የፌደሬሽን ምክር ቤትና የህዝብ ተወካዮች ምክር በቶችን ያቀፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ147ኛው ዓለም አቀፍ ፓርላሜንታዊ ኅብረት ጉባኤ በአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

👉ኢትዮጵያ ፈተናን ወደ ድል የሚቀይር የአሸናፊ ሠራዊት ባለቤት ናት መሆኗ የኤፌዲሪ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡

👉የባሕር በር ባለቤትነት በወደብ ተጠቃሚ ሀገሮች መካከል ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ይበልጥ ለማሳደግ ይረዳል ሲሉ የፐብሊክ ፖሊሲና ምጣኔ ሀብት ምሑሩ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

👉ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከ8 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ።

👉”አጋርነት ለማህበረሰብ እድገት” በሚል መሪ ቃል 4ኛ ዙር የማህበረሰብ ምክክር መድረክ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡