የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዞኑ ፋይናንስ አግልግሎት አሰጣጥ ላይ እየገጠሙ ያሉ ችግሮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የጋራ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር በዲላ ከተማ ተካሂዷል።
ውይይቱን የመሩት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ ጤካሞ በ2016 አጠቃላይ በጀትና በፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ለባለድርሻ አካላት አብራርተዋል።
አምና በተሰበበው ገቢ ላይ ከ8 መቶ ሚሊየን ብር በላይ መጨመሩን የገለጹት ኃላፊ አሁን ላይ እየገጠሙን ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም መዋቅር ገቢ አሟጦ መሰብሰብ አለበት ነው ያሉት።
አሰተያየታቸውን የሰጡት ተሳታፊዎችም እንደሀገር የጥሬ ገንዘብ እጥረት መኖሩን አንስተው እነዚህ ችግሮችን ለመቋቋም ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ሁሉም የባለድርሻ አካላት መፍትሔ ነው ያሏቸውን ሀሳቦች እያነሱ በጥልቀት ተወያይተዋል።
ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ጎበና – ከፍስሃገነት ጣቢያችን
More Stories
ገቢን በተገቢው በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በተገቢው መመለስ እንደሚገባ ተገለጸ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 የግብር ወቅት ከደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለጸ
የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የዘርፉን ተግባራት በተገቢው ለማሳካት ከምንጊዜውም በተሻለ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ