ዛሬ የተከፈተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ምቹ መዳረሻ የሚያደርጋትን በናሙና እንዲያዩ ዕድል ይሰጣል- ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ
ሀዋሳ፡ መስከረም 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዛሬ የተከፈተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ምቹ መዳረሻ የሚያደርጋትን በናሙና እንዲያዩ ዕድል ይሰጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ብዙ ታሪክ፣ ቅርስ ፣ባህል ፣ የተፈጥሮ ስጦታዎች ፣አዕዋፍ ፣የዱር አራዊት እና ሊጎበኙ የሚችሉ ድንቅ ሁነቶች እንዳሉን ግምት ውስጥ በማስገባት ከኢኮኖሚው ዘርፍ ዋና ምሦሦዎች አንዱ የቱሪዝም ሴክተሩ ነው።”ብለዋል፡፡
“ዛሬ የተከፈተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ምቹ መዳረሻ የሚያደርጋትን በናሙና እንዲያዩ ዕድል ይሰጣል። ያለንን ዐቅም ለማውጣት፣ ኢትዮጵያን የብዙ ውበቶች እና ግኝቶች መዳረሻ አድርጎ ለማስተዋወቅ እና ለማገልገል ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራችሁ ያላትን ሀብት ማየት፣ ማውጣት፣ ማስተዋወቅ እና ማገልገል ይጠበቅባችኋል።” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/