የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረቡለትን እቅዶች መርምሮ አጸደቀ
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እያካሄደ ባላው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ የቀረቡለትን እቅዶች መርምሮ አጽድቋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔውም የሕገ-መንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ፣ የመንግስታት ግንኙነት የዲሞክራሲ አንድነትና የሕገ-መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ፣ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴና የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ያቀረቡት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን እቅዶች ካደመጡ በኋላ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የየቋሚ ኮሚቴዎቹ አመራሮችም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች የሥራ ሀላፊዎች በጉባዔው መገኘታቸውንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ትላንት መካሄዱ ይታወቃል።

More Stories
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቀ
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም እያካሄደ ነው
የላስካ ከተማ ነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ