በ6ኛው የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በመክፈቻ ንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

በ6ኛው የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በመክፈቻ ንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉ጉልበታችንና ጊዜያችንን ከትላንት ይልቅ በነገ ላይ እናውል፡፡ ይህ የዚህ ትልቅ ትውልድ ሃላፊነት ነው፡፡

👉እኛ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ትብብር በርካታ ችግሮችንና ተግዳሮቶችን ተሻግረናል፤ ከእኛም በማለፍ ለሌሎች ጥበብና ስልጣኔን ማካፈልም ችለናል፡፡

👉መንግስት ባለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ ባዘጋጀው የ10 ዓመት የልማት እቅድ አፈጻጸም በሁሉም የእድገት አመላካች ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግቧል ፡፡

👉በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረውን ደም አፋሳሽ ጦርነት የሰላም ስምምነት አድረገናል፤ ለአፍሪካዊ ችግር የአፍሪካዊ መፍትሔ የሚለው መርህ በአህጉራችን ውጤታማ መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል፡፡

👉ያደሩና ለዘመናት የነበሩ የሀሳብ ልዩነቶችን ለማስታረቅና ለማቀራረብ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቋቁመናል፡፡

👉የቀደሙ ክፍተቶችን ዝንፈቶችን በማረም የወደፊት ዕድላችንን ተመካክረን ለማቅናት የተሻለች ኢትዮጵያን የመፍጠር እድል በእጃችን ነው፡፡

👉መንግስት ዘርፈ ብዙ የዕድገት አማራጮችን ነድፎ እየሰራ ነው፤ በዚህም ኢኮኖሚያችን ከገባበት ቅርቃር እየወጣ በለውጥ አዙሪት ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ተከታታይ እድገት እንዲመዘገብ አስችሏል፡፡

👉ባለፈው አንድ አመት 7.5 በመቶ ጥቅል ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ተመዝግቧል፡፡

👉መንግስት የሀገሪቷን ሀገረ መንግስት ለማረጋገጥ ባለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ ባዘጋጀው የ10 ዓመት የልማት እቅድ አፈጻጸም በሁሉም የእድገት አመላካች ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡

👉የትላንት ታሪክ የአብሮነት መገንቢያ እንጂ የልዩነት መነሻ መሆን የለበትም፡፡

👉ያለፈው ዓመት የዓባይ ግድብ 4ኛ ዙር የውኃ ሙሌት እና ከ90 በመቶ በላይ ግንባታው መጠናቀቁን የሰማንበት ዓመት ነበር፡፡

👉ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 160 ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

👉ባለፉት ዓመታት የታዩ ውጤቶችን በማስቀጠል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከምርት አቅርቦት የሚመነጭ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ይሰራል፡፡

👉የሀገር ውስጥ ንግድ ስርዓትና ጥራት በማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል፡፡

👉በመጭው 3 ዓመት ውስጥ 9.15 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚሰራ ይሆናል፡፡