የረዥም ዓመታት የጠምባሮ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ በልዩ ወረዳ መዋቅር መደራጀቱ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በምሥረታ በዓሉ የተገኙ የብሔረሰቡ ተወላጅ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ
መዋቅር ብቻውን ውጤት ሊሆን ስለማይችል የህዝብ ለህዝብ ትስስርና አንድነትን ለማጠናከርና የአከባቢውን ልማት ለማፋጠን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስተያየት ሰጪዎቹ አመላክተዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ምስረታ በዓል ላይ አግኝተን ካነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች መካከል መካካል በፌዴራል ማረሚያ ኮሚሽን የመሠረታዊ ፍላጎትና አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ በሽር በራታ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ አቶ ከበደ ሶማኖና አቶ ተመስገን በርገኖ በሰጡት አስተያየት የጠምባሮ ህዝብ ለበርካታ ዓመታት ህገ መንግሰታዊ መብቱን ለማስጠበቅ ሲያደርግ የነበረው ሰላማዊ ትግል ፍሬ አፍርቶ በልዩ ወረዳ መዋቅር መደራጀቱ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች እንዳሉት ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ ራሱን በራሱ ማስተዳደር፣ ማልማትና ያለውን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ለልማት እንዲነሳሳ ከማድረግ አንፃር ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ሌሎቹ አስተያየት ሰጪዎች አቶ ዳዊት ዳለቾ፣ ወ/ሮ ትዕግሥት በላቸው እና ወ/ሮ በላይነሽ ተሰማ እንደተናገሩት የልዩ ወረዳ መዋቅር ህዝቡ በቅርበት የፍትህና ሌሎችንም አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል።
የልዩ ወረዳ መዋቅር ብቻውን ውጤት ሊሆን ስለማይችል ቀጣይ የህዝብ ለህዝብ ትስስርና አንድነትን በማጠናከር የአከባቢውን ልማት ለማፋጠን በትኩረት ሊሠራ ይገባል ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ።
የልዩ ወረዳው አመራሮች ያለ ልዩነት የህዝቡን አንድነት በማጠናከር፣ ለልማት በማነሳሳትና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም አቀናጅተው በመምራት ውጤትን በተግባር ለማሳየት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ለአከባቢው ልማት አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ አመራሩና መላው ህዝብ በተለያዩ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ ያሉ የአከባቢውን ተወላጆች በማቀናጀት ለአከባቢው ልማት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በምስረታው ወቅት አጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች ለልዩ ወረዳው ያደረጉትን መልካም ድጋፍ በማድነቅ ልዩ ወረዳ መሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው በመጠቆም።
ዘጋቢ: ሙሉነሽ ለማ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ