የኮሬ ዞን አስዳደር በይፋ መመስረቱ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኮሬ ዞን የሽግግር ምክር ቤት 1ኛ መሥራች ጉባኤውን አካሂዷል።
በምሥረታው የብሔረሰቡ ሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ተገኝተው በፀሎትና በቡራኬ ጉባኤውን ከፍተዋል።
ጉባኤው የኮሬ ዞን የሽግግር ምክር ቤት አስመራጭ ኮሚቴ ሰይሞ የነበረ ሲሆን፥ አቶ እንግዳ በቀለ፣ ወ/ሮ አሰበች አሸናፊ እና አቶ ታሪኩ ገረሙ ጉባኤውን መርተዋል።
የኮሬ ዞን የሽግግር ምክር ቤት 1ኛ መሥራች ጉባዔ የዞኑ ስያሜና የዞኑ ፊት አመራሮች ሹመት የጸደቀ ሲሆን፦
1. አቶ ታረቀኝ በቀለ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ፣
2. አቶ አሰታረቀኝ አንደባ ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ
3. የተከበሩ ወ/ሮ አካላት በቀለ ዋና አፈጉባዔ
4. የተከበሩ አቶ ዳኛቸው ሰብስቤ ምክትል አፈጉባዔ
5. አቶ ጢሞቴዎስ በቀለ የዞኑ የመንግት ዋና ተጠሪ
6. አቶ ብርቅነህ ጌታሁን የመንግሥት ረዳት ተጠሪ
7. አቶ አዳሙ አንኪላ የመንግሥ ረዳት ተጠሪ
8. አቶ ሙሉቀን በቀለ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዋና ፕሬዝዳንት
9. አቶ ቢኒያም ገ/ኢየሱስ ከፍተኛ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ተሹመዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ ለጉባኤው ንግግር ባደረጉበት ወቅት በሠላማዊ መንገድ ሲጠየቅ የቆየው የዞን ምሥረታ ማድረግበመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ ለቀጣይም የህዝብን አደራ በታማኝነት እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የቀድሞው የልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የአሁኑት የደቡብ ኢትዮጵያዊ ሠላም ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ ለአዲሱ የኮሬ ዞን አስተዳደሪ ለአቶ ታረቀኝ በቀለ ርክክብ አድርገዋል።
ጉባኤው አስተያየት ከሰጡ የምክር ቤት አባላት መካከል አቶ ማተቤ ዘርፉ፣ ወ/ሮ ዳመነች ስልቅቴና ሌሎችም አዲሱ ተሿሚዎች ጠንክረው እንዲሠሩ መክረዋል።
በመጨረሻም በዞኑ ስያሜና አዲሱ የወረዳ ማዕከላት ላይ የዞኑ የመንግት ዋና ተጠሪ አቶ ጢሞቴዎስ በቀለ አቅርበው ውይይት ተደርጎበት የዞኑ ስያሜ “የኮሬ ዞን” በሚል እና የወረዳ ማዕከላት “ካርማ” እና “ደርባ” ሆኖ ጸድቋል።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከፍስሃገነት ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ