ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! – አቶ አለማየሁ ባውዲ
ሀዋሳ፡ መስከረም 16/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍ እና የመከባበር እሴቶቻችን ማሳያ ለሆነው የመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ የሚከበር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በህዝቦች መካከል የአብሮነት የመኖር እሴቶችን የሚያጎለብት እንዲሁም የአንድነትና የመቻቻል መንፈስን የሚያጠናክር ነው።
በዓሉ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥና አንድነት መጽናት ከመቼውም ጊዜ በላይ የምንተጋበትና ትስስራችንን የበለጠ የምናፀናበት በዓል እንዲሆንም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መልካም የመስቀል በዓል!

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ